የክላርክ ካውንቲ የትምህርት ቤቶች ዲስትሪክት ለእንግሊዝኛ ቋንቋ ተማሪዎች የነደፈው መሪ ዕቅድ አፈጻጸም በታቀደለት መስመር ወደ ፊት መንቀሳቀሱን ቀጥሏል።
በግንቦት 2016 በትምህርት ቤት አመራሮች ቦርድ የጸደቀው ዕቅድ፣ የመጀመሪያ ቋንቋቸው እንግሊዝኛ ያልሆኑ ተማሪዎችን ክህሎት እና የብቃት ደረጃ ለማሻሻል አምስት ስትራቴጂካዊ አላማዎችን ያካተተ ነው ።
እነዚህ አምስት አላማዎችም የሚከተሉት ናቸው።
- የኢ.ኤል.ኤልን የትምህርት ጥራት ማሻሻል
- የኢ.ኤል.ኤል የመመሪያ መርሃ ግብር አማራጮችን ማሰባጠር
- ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የኢ.ኤል.ኤል አስተማሪዎችን መቅጠር፣ ማቆየት እና ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ማድረግ
- የሁሉንም እንግሊዝኛ ቋንቋ ተማሪዎች የተለያዩ ፍላጎቶች ግምት ውስጥ የሚያስገባ እና ቤተሰቦቻቸውን የሚያካትት ምቹ ሁኔታ እና ባህል ማዳበር
- በትምህርት ቤቶች እና በተለያዩ መምሪያዎች ውስጥ ፍትሃዊ የመማር ማስተማር ዕድሎች እንዲኖሩ፣ ፖሊሲዎችን፣ መዋቅሮችን እና የአፈጻጸም ልምዶችን መስመር ማስያዝ